lirikcinta.com
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

lirik lagu amen – teddy afro

Loading...

ቀን በአደባባይ በከተማ
አገር እያየ እየሰማ
ልቤን በውበት ድንገት ሰወርሽው

እስከኔው ጨምረሽ ወይ አልወሰድሽው

ቀን በአደባባይ በከተማ
አገር እያየ እየሰማ
ልቤን በውበት ድንገት ሰወርሽው
እስከኔው ጨምረሽ ወይ አልወሰድሽው

ጋልቦ በገራው ፈረሰ ርቆ ተጓዥ ለጉዳይ
እንዴት ይጥላል ልቡን በድንገት ከአደባባይ
ወይ ካደረግሽው ማርከሽ የፍቅርሽ ሟች ተረኛ
በቃ አሳርፊው ልቤን አታስጨንቂኝ ተይኛ

እርፍ ይበል ልቤም ቁርጡን አውቆ
ቁርጡን አውቆ
እንዴት ይችላል ታዲያ እንዲህ ተጨንቆ
እንዲህ ተጨንቆ
የወደደ ታሞ ባይዝ አልጋ
ባይዝ አልጋ
ቆሞ ሲሔድ ሁሌም ከራሱጋ
ነው እያወጋ

እንደድንገት ልቤ ድንግጦ
ጥሎኝ ሔደ ከኔ አንቺን መርጦ
የደነገጠው ልቤን ወስደሽው
በይ ንገሪኝ የት አደረግሽው
ይሔኔ ልቤን ጥለሽ ይሆናል
በዚህ ግዜ ማን ይታመናል
የያዘኝ ፍቅርሽ የረታው አቅሜን
ባንቺም ደርሶ ምነው ባልኩ አሜን

አሜን አሜን አሜን………….ኸረ አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን………….ኸረ አሜን አሜን
ልቤን እንዳጣው አቅሜን
ባልኩኝ ፍቅር ይዞሽ አሜን
አሜን አሜን ……………….

ቀን በአደባባይ በከተማ
አገር እያየ እየሰማ
ልቤን በውበት ድንገት ሰወርሽው
እስከኔው ጨምረሽ ወይ አልወሰድሽው

ቀን በአደባባይ በከተማ
አገር እያየ እየሰማ
ልቤን በውበት ድንገት ሰወርሽው
እስከኔው ጨምረሽ ወይ አልወሰድሽው

እንዴት ሳያጉረመርም ዝናብ ይጥላል ሰማይ
ድንገት አራሰው ልቤን ውበትሽ መሥሎ ፀሀይ
ሀሳብ ቀላቅሎ ሲጥል እኔስ ብርዱ ገደለኝ
ምነው ወይ አዝኖ ልብሽ ከፍቅርሽ ቢያስጠልለኝ

እትት ሲል ጐኔም አንችን ናፍቆ
አንችን ናፍቆ
እንዴት ይችላል ታዲያ እንዲ ተጨንቆ
እንዲ ተጨንቆ
ዘምቦ በኔ ፍቅርሽ እስኪያባራ
እስኪያባራ
ምነው ቢኖር ልቤ ካንቺ ጋራ
ባንድ ጣራ

እንቺ ምክር ካንቺ ባላውቅም
ሀይለኛ ነው ፍቅር አይናቅም
በዚህምድር የፈሩት ደርሶ
ስንት አይተናል የናቁት ወርሶ
የናቁት ወርሶ ብድር ሲመልስ
ያስጨንቃል መቼም አያድርስ
እኔ በፍቅርሽ እንዳጣው አቅሜን
ባንቺም ደርሶ ምነው ባልኩ አሜን

አሜን አሜን ……….ኸረ …አሜን አሜን
አሜን አሜን ……….ኸረ …አሜን አሜን
ልቤን እንዳጣው አቅሜን
ባልኩኝ ፍቅር ይዞሽ አሜን
አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን

lirik lagu lainnya :

YANG LAGI NGE-TRENDS...

Loading...