lirikcinta.com
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

lirik lagu kidest – deacon zemari kedametsega yohanis

Loading...

በኩርናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእርሷም ደስ ይበለን

በሰንበተ ክርስቲያን
በኩርናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእርሷም ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን
በዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና
መልካም ስራ የሚሰራባት ሰንበት ቅድስት ናትና
ከጨለማ ብርሃንን ከመገዛት ነፃነት
እግዚአብሔር ይህን ሰጠን ደስ ይበለን በሰንበት
በኩርናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእርሷም ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን
ለአብርሃም ተገልጣለች ለሙሴም በደብረ ሲና
በነቢያት የታወቀች ሰንበት ደኃራዊት ናትና
በሳምንቱ ሰለጠነች ተሰበከች በሐዋርያት
ሃሌሉያ ዕለተ ሰንበት ተሰጠችን ልናርፍባት
በኩርናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእርሷም ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን
በእልልታ እንሞላ እንደ ነቢዩ አሳፍ
በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ
በመቅደሱ ናቸውና ቅዱስነትና ግርማ
ቅዳሴያችን ይሰማልን ከምድር እስከ ኢዮርራማ
በኩርናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእርሷም ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን
እግዚአብሔር አብ የባረካት
እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት
ከዕለታት ሁሉ መርጦ መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያደረጋት
በእርሷ ሀሴት እናድርግ እናክብራት እንድንከበር
ከደጀ ሰላሙ ታዛ ከመቅደሱ እንሰብሰብ
በኩርናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእርሷም ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን
በኩርናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእርሷም ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን

lirik lagu lainnya :

YANG LAGI NGE-TRENDS...

Loading...