lirikcinta.com
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

lirik lagu yene set (የኔ ሴት) – znar zema (ዝናር ዜማ)

Loading...

[አማኑኤል፡-]
እንዲህ ነው ሕይወት ግሩም ቀለም
ሁሉም ለየቅል የዓለም ጣ’ም
ምርጫ እንደ መልኩ ፀባይ ዓይነቱ
ብዙ ነው ለካ የፍላጎቱ

(ኦዉ-ሁ) የ’ሱ ሴት መልከ መልካም
(ኦዉ-ሁ) የ’ሱ ሴት ሰናይ ፀባይ
(ኦዉ-ሁ) የ’ሱ ሴት እንደ ምርጫው
(ኦ-ኦ-ዉ) የ’ሱ ግን ምርጫ አቻው

[ሮቤል፡-]
ቃል ሳይወጣት ‘ባይኗ ቋንቋ ሳታወራ
ዝምተኛን አዛኝ ጨዋ የ’ውነት ፍቅሯ
ኧረ እንዴት እንዴት እንዴት ያለች
የማትጠገብ ነች
ኧረ እንዴት እንዴት እንዴት ያለች
የማትጠገብ ነች

[አማኑኤል፡-]
(ኦዉ-ሁ) የ’ሱ ሴት መልከ መልካም
(ኦዉ-ሁ) የ’ሱ ሴት ሰናይ ፀባይ
(ኦዉ-ሁ) የ’ሱ ሴት እንደ ምርጫው
(ኦ-ኦ-ዉ) የ’ሱ ግን ምርጫ አቻው

[እስክንድር፡-]
ፍቅሯን ስትገልጥ ሰው አትፈራ ቦታም አትመርጥ
ታይታ ‘ማታውቅ ሁሌ አንድ ናት አትለወጥ
ቀበጥ ናት ብለው ቢሰይሟት
ከልቧ አፍቃሪ ናት
ቀበጥ ናት ብለው ቢሰይሟት
ከልቧ አፍቃሪ ናት

[አማኑኤል፡-]
(ኦዉ-ሁ) የ’ሱ ሴት መልከ መልካም
(ኦዉ-ሁ) የ’ሱ ሴት ሰናይ ፀባይ
(ኦዉ-ሁ) የ’ሱ ሴት እንደ ምርጫው
(ኦ-ኦ-ዉ) የ’ሱ ግን ምርጫ አቻው

[ደሳለኝ፡-]
ኩርፊያዋ ብዙ ፍቅር የገባት
ልታይ የማትፈቅድ የ’ኔን መከፋት
እኔ ‘ምወደው ጣፋጭ አንደበት
አይቼ አላውቅም እንደ’ሷስ ዓይነት

[ሮቤል፡-]
(አ-ሃ) የ’ኔ ሴት ዝምተኛዋ

[እስክንድር፡-]
(እ-ህ) የ’ኔ ሴት ቀበጥ የዋህ

[ደሳለኝ፡-]
(ኤ-ሄ) የ’ኔ ሴት አኩራፊዋ

[አማኑኤል፡-]
ሁሉም ምርጫው ልዩ ነው ለካ

[በጋራ፡-]
የየሰው የፍላጎቱ
ብዙ ነው ምርጫው ዓይነቱ
ከሰው ሰው የፍላጎቱ
ብዙ ነው ምርጫው ዓይነቱ
የየሰው የፍላጎቱ
ብዙ ነው ምርጫው ዓይነቱ
ከሰው ሰው የፍላጎቱ
ብዙ ነው ምርጫው ዓይነቱ

lirik lagu lainnya :

YANG LAGI NGE-TRENDS...

Loading...